Fana: At a Speed of Life!

ዩ ኤስ አይ ዲ በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 152 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጅት (ዩ ኤስ አይ ዲ) በትግራይ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 152 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ።

ይህም ድርጅቱ በትግራይ ክልል በቅርብ ጊዜ ያደረገውን ድጋፍ ወደ 305 ሚሊየን ዶላር ከፍ አድርጓታል።

ድጋፉ በክልሉ ህግ የማስከበር እርምጃውን ተከትሎ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የንፁህ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ፣ ለአስቸኳይ የህክምና እና የጤና ድጋፍ እንዲሁም ለመጠለያ ግንባታ እንደሚውል ነው ኤጀንሲው ያስታወቀው።

ድርጅቱ ያደረገው ድጋፍ ለሴቶችና ህፃናት የስነ ልቦና ድጋፍ መስጠትና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የተለየዩ ህፃናትን ማገናኘትን ጨምሮ ተጋላጭ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከለላ ለመስጠት እንደሚውልም ነው የገለፀው።

የህይወት አድን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው 3 ሚሊየን ዜጎች ድጋፍ እንደሚደረግ ያስታወቀው ድርጅቱ ከዚህ ቀደም የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ ቡድን ወደ ክልሉ ማሰማራቱን አስታውሷል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.