Fana: At a Speed of Life!

በ85 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዚያ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን በኩታበር ወረዳ በ85 ሚሊየን ብር የተገነባው እናት የዱቄት ፋብሪካ ተመረቀ፡፡
ፋብሪካው አሁን ላይ በቀን ከ500 ኩንታል በላይ ሲያመርት በሙሉ አቅሙ ማምረት ሲጀምር 1 ሺህ ኩንታል የቦቆሎ ዱቄት የሚያመርት መሆኑን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ አቶ ይማም አሊ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ፋብሪካው 150 ለሚሆኑ ሰዎች የስራ እድል መፍጠር የቻለ ሲሆን ሙሉ ለሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ከ300 በላይ ለሆኑ ሰዎች የስራ እድል ይፈጥራል ብለዋል።
የተገነባው ፋብሪካ በቆሎን በመፍጨት እና እሴት በመጨመር ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ መናገራቸውን ከደቡብ ወሎ ዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.