Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ የካንሳር ሃኪሞች አንዱ የነበሩት ዶ/ር አይናለም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ በካንሰር ህክምና ዘርፍ በማግልገል ቀዳሚ የነበሩት ዶክተር አይናለም አብርሃ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ በመምህርነት እና በካንሰር ሕክምና ዘርፍ ያገለግሉ የነበሩት ዶክተር አይናለም አብርሃ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም ሕይወታቸው ማለፉን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል።

የዶክተር አይናለም አብርሃ ሕልፈት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ለሀገሪቱ ትልቅ ጉዳት ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና የገለፁት፡፡

ዶክተር አይናለም አብርሃ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመምህርነትና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በካንሰር ሕክምና ከፍተኛ ባለሙያነት እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የካንሰር ሕክምና ማዕከል ሐላፊ በመሆን ለበርካታ አመታት አገልግለዋል።

ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ እና በራሳቸው ስም በዶክተር አይናለም አብርሃ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጃ ዱጉማም በዶክተር አይናለም አብርሃ ህልፈተ ህይወት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለፅ  ከቀዳሚዎቹ  ጥቂት የካንሳር ሃኪሞች መካከል አንዱ ነበሩ ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.