Fana: At a Speed of Life!

ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር የአቋም መለኪያ ጨዋታ ሊያደርጉ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን (ሉሲዎቹ) ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር የመጀመሪያውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነገ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚያደርጉ ተገለፀ፡፡
ጨዋታው በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የሃገር አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ምክንያት ነገ ከምሽቱ 12 ሠዓት ከ30 እንደሚደረግ ታውቋል፡፡
ሉሲዎቹ ከመጋቢት 26 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በካፍ የልህቀት ማዕከል ቆይታ በማድረግ ልምምዳቸውን እየሰሩ በጥሩ ዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.