Fana: At a Speed of Life!

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ 195 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንሰ ኮሌጅ ያሰለጠናቸውን 195 የህክምና ዶክተሮች አስመረቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው ካስመረቃቸው መካከል 38ቱ በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም የሰለጠኑ እንደሆኑ ተገልጿል።

ሁለት ተመራቂዎች ደግሞ ከኖርዌይ በርገር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በሶስተኛ የህክምና ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ መሆናቸውን የኮሌጁ ኤክስኪዩቲቨ ዳይሬክተር ዶክተር አንተነህ ጋዲሳ ለኢዜአ ገልፀዋል።

ዩኒቨርሲቲው ዶክተሮችን ዛሬ ሲያስመርቅ ለ12ኛ ጊዜ ሲሆን ስፔሻሊስቶችን ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ መሆኑ ታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.