Fana: At a Speed of Life!

የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በአዊ ብሄረሰብ ዞን በመስኖ የለማ ስንዴን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፋግታ ለኮማ ወረዳ በመስኖ የለማ ስንዴን ጎበኙ።

የመስኖ ልማቱ የአካባቢውን እምቅ የግብርና አቅም ጥቅም ላይ በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።

በቀጣይም አርሶ አደሩ በዘመናዊ መንገድ የመስኖ ልማትን በመተግበር የተሻለ ገቢ እንዲያገኝና ኑሮውን እንዲያሻሽል የክልሉ መንግስት በትጋት እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በወረዳው በ960 ሄክታር ማሳ ላይ 610 አርሶ አደሮችን ያሳተፈ የመስኖ ስንዴ ልማት ስራ እየተከናወነ ሲሆን ጉብኝት በተካሄደበት ዝንቢሬ ቀበሌ 290 ሄክታር ማሳ በኩታ ገጠም ስንዴ በመስኖ እየለማ ነው።

በብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ 5 ሺ 700 ሄክታር ማሳ ላይ ስንዴ ሰብል በመስኖ እየለማ ሲሆን አጠቃላይ በክልሉ ደግሞ ከ13 ሄክታር በላይ ማሳ በስንዴ መሸፈኑን ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.