Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛሳምንት የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን አሸነፈ፡፡

የኢትዮጵያ ቡና ሰበታ ከተማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ነው ያሸነፈው፡፡

ለኢትዮጵያ ቡና ሁለቱን ግቦች አቡበከር ናስር ሲያስቆጥር ለሰበታ ከተማ ብቸኛዋን ግብ ፉዓድ ፈረጃ አስቆጥሯል፡፡

ፕሪምየር ሊጉን ፋሲል ከነማ በ16 ጨዋታዎች 41 ነጥቦችን ሰብስቦ እየመራ ይገኛል፡፡

ዛሬ ሰበታ ከተማን ያሸነፈው የኢትዮጵያ ቡና በ17 ጨዋታዎች 33 ነጥቦችን ሰብሰቦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡

ባህርዳር ከተማ በ16 ጨዋታዎች 29 ነጥቦችን ሰብስቦ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

 

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.