Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽንና ሁዋዌይ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 4፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌድሪ ሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና በቴሌኮም መሠረተ ልማት ዋና አቅራቢነት የሚታወቀው ሁዋዌይ በኢትዮጵያ አይሲቲ ተሰጥኦ ሥነ ምህዳርን ለማልማት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል ፡፡

ሥነ ምህዳሩ ተማሪዎች እና ባለሙያዎችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ማረጋገጫ እንዲያገኙ እና በቴሌኮም እና በአይቲ ዘርፍ የሚኖራችውን የወደፊት ጉዞ እንዲያዳብሩ የሚረዳ ነው።
ትብብሩ ሲተገበር የሁዋዌይ ሥልጠና እና የብቃት ማረጋገጫ አዳዲስ ተመራቂዎች ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ከማገዙም በላይ በኢንዱስትሪው ውስጥ ለሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች አዳዲስ ክህሎቶችን ያስገኛል ፡፡

በኮሚሽኑ የክህሎት ማዳበር እና የሥራ ፈጠራዋች ክትትል እንዲሁም የሥራ ስምሪት መርሃ ግብሮች አማካኝነትም በአገር ውስጥ ላለው የሥራ ኃይል ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዕውቅና ይሰጣል ፡፡

የሥልጠናና የብቃት ማረጋገጫ መርሃግብሩ ለሶስት ዓመታት የሚቀጥል ሲሆን፤ በመጀመሪያው ዓመት ለ800፣ በሶስት ዓመታት ደግሞ ለ7ሺህ ወጣቶች የብቃት ማረጋገጫ ይሰጣል ተብሏል ፡፡

ለ3ሺህ ወጣቶች ሶስት ዓመታት በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ ውስጥ የሥራ ዕድሎችን የማመቻቸት እቅድ መያዙም ነው የተገለጸው ።

በተጨማሪም በመጀመሪያ ዓመት 40 ዩኒቨርስቲዎች ላይ ግንዛቤን ለማሳደግ ፣ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ ሥልጠናዎችን እና የማዕከሉን ተመራቂዎች ቁጥር ለማሳደግ ያለመ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት ውስጥ 100 ዩኒቨርስቲዎችን እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማትን ለመሸፈን ያለመ መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለንⵑ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.