Fana: At a Speed of Life!

ከ800 በላይ ጥይቶችን በበቆሎ ውስጥ ደብቆ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ800 በላይ ጥይቶችን በበቆሎ ውስጥ ደብቆ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገለፀ።

ግለሰቡ ወንጀሉን የፈፀመው በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7  ልዩ ቦታው አውቶቡስ ተራ ትንሿ መናኸሪያ ግቢ  ውስጥ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ግለሰቡ በሁለት ከረጢት በያዘው በቆሎ ውስጥ 200 የብሬን እና 668 የክላሽ ንኮቭ በአጠቃላይ 868 ጥይቶችን ቀላቅሎ በመደበቅ በተሽከርካሪ ጭኖ ለማዘዋወር ሲንቀሳቀስ በወቅቱ በስራ ላይ በነበሩ የመናኸሪያው የስነ-ስርዓት ተቆጣጣሪዎች ጥርጣሬ በቁጥጥር ስር ሊውል መቻሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የአውቶቡስ ተራ  መናኸሪያ ሥነ ስርዓት ተቆጣጣሪዎች ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ሲፈፀሙ የነበሩ ሕገ- ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እና ሌሎች ወንጀሎችን በመቆጣጠርና እጅ ከፍንጅ በመያዝ ውጤታማ ስራ መስራታቸውን  ኮሚሽኑ አስታውሷል።

ኮሚሽኑ አያይዞም ይህንን ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ  በመጠየቅ ለከተማዋ ሰላም እያበረከቱት ላለው አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.