Fana: At a Speed of Life!

ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንደሚወጡ  በተለያዩ  ክልሎች ላይ እየሰሩ የሚገኙ የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት  ገለጹ።

ከፋና ጋር ቆይታ ያደረጉ በደቡብና በሲዳማ ክልሎች የሚገኙ የሲቪል ማህበራት አመራሮችና አባላትም ተቋማቸው ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ ሰባዊ መብቶች እንዲከበሩ የሚሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ምርጫውን ለመታዘብም እድሉን ያገኙ የሲቪል ማህበራትም አባላቶቻቸውን በማሰልጠንና ከየትኛውም የፖለቲካ ፖርቲ ነፃ በሆነ መልኩ በገለልተኛነት ለመታዘብ ዝግጁ መሆናቸውን ለጣቢያችን ገልፀዋል

ህዝቡም ድምፅ በመስጠት መብቱን በአግባቡ ሊጠቀም ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች ሴቶች ማህበራት ሀዋሳ ቅርንጫፍ አስተባባሪ ወይዘሪት ሰላማዊት ካሳ÷ ማህበራቸው በተለያዩ የሀገሩቱ አካባቢዎች እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ማህበራት የሚጠበቅብንን ሀላፊነት በአግባቡ መወጣት አለብን ሲሉም ተናግረዋል ።

አቶ ዮናታን አማኑኤል የፍቅር በህይወት ወላጅ ያጡ ህፃናትና ወጣቶች ተራድኦ ድርጅት አስተባባሪ በበኩላቸው÷ ምርጫውን ገለልተኛ በሆነ መልኩ ለመታዘብ መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል።

አያይዘውም ህዝቡም መብቱን እንዲጠቀም እንሰራለን ሲሉ ተናግረዋል።

በብርሃኑ በጋሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.