Fana: At a Speed of Life!

ለምስራቅ አፍሪካ አባል ሃገራት ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል አባል ሃገራት ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች በሰላም ማስከበር ቅድመ ስምሪት ዙሪያ ስልጠና መሰጠት ተጀመረ።
በስልጠናው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከዩጋንዳ ፣ ከኮሞሮስ ፣ ከጅቡቲ ፣ ከሶማሊያ ፣ ከኬኒያ እና ከብሩንዲ የተውጣጡ ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ስልጠናው በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም የሚቆይ መሆኑ ተገልጿል።
የምስራቅ አፍሪካ ተጠባባቂ ሃይል ዳይሬክተር ብርጋዴል ጀነራል ጌታቸው ሽፈራው እንዳሉት ስልጠናው ለቀጣናው የጋራ ሰላም፣ ዕድገትና የጋራ ልማት ጉልህ አስተዋጽኦ አለው ማለታቸውነር ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለንⵑ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.