Fana: At a Speed of Life!

በማይካድራ በተፈጸመው ወንጀል ተሳትፎ አላቸው በተባሉ 21 ተጠርጣሪዎች ላይ የቅድመ ምርመራ ምስክር መሰማት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በማይካድራ በተፈጸመው ወንጀል ለበርካታ ንጹሀን ዜጎች ግድያ እና ሴቶችን በማስደፈር በቀጥታ ተሳትፎ አላቸው በተባሉ 21 ተጠርጣሪዎች ላይ የቅድመ ምርመራ ምስክር መሰማት ተጀመረ።
በዛሬው እለት የዐቃቤ ህግ ቅድመ ምርመራ ምስክሮች መሰማት የጀመሩት በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው።

ቅድመ ምስክሮቹ የተሰሙት በጃንቦ ብርሀነ ስም በተከፈተ መዝገብ ስር በሚገኙ 21 ተጠርጣሪዎች ላይ ነው ተብሏል።

ተጠርጣሪዎቹ ጥቅምት 30 ቀን 2013 ዓ.ም ከህወሓት ጸረ ሰላም ቡድን ጋር በመቀናጀት የአማራ ብሄር ተወላጆችን በመለየት በርካታ ንጹሃን ዜጎችን በመግደል በቀጥታ ተሳትፎ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

በዚህ ወንጀል ከ10 በላይ ሴቶች እንዲደፈሩ በማድረግ፣ ከ120 በላይ ንጹሀን ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት በማድረስ እንዲሁም በአካባቢው የሚገኝና 17 ሚሊየን 620 ብር የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ከዚህ በፊት በጊዜ ቀጠሮ ችሎት በፖሊስ መገለጹ የሚታወስ ነው።

ዐቃቤ ህግ ማስረጃ ለማቆየት በተጠርጣሪዎቹ ላይ ዛሬ ካቀረባቸው 11 ምስክሮች ውስጥ ሶስቱ የምስክርነት ቃላቸው ተሰምቷል።

ችሎቱ ቀሪ ምስክሮችን ለመስማት ለነገ በይደር ቀጠሮ ሰጥቷል።

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.