Fana: At a Speed of Life!

ተሻሽሎ የቀረበዉ የሀገር አቀፍ የስፖርት ማህበራትን ለማቋቋም የተዘጋጀዉ መመሪያ ፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት ስብሰባ በስካይ ላይት ሆቴል ዛሬ አካሂዷል፡፡
በስብሰባው የብሔራዊ ስፖርት ምክር ቤት የስፖርት ማህበራት ስለሚቋቋሙበት ረቂቅ መመሪያ ላይ ሰፊ ዉይይት በማካሄድ በሙሉ ድምፅ አፅድቋል ።
በዚህም መሠረት በተለይ የክልል ስፖርት ኮሚሽነሮች በድምፅ ከሚሳተፋ ገለልተኛ ሆነው ስፖርቱን ቢደግፋ የተሻለ ነው የሚለው ሀሳብ ሚዛን በመድፋቱ ያለድምፅ እንዲሳተፋ መግባባት ላይ ተደርሷል ።
የስፖርት ማህበራት የስራ አስፈፃሚዎች የቆይታ ዘመን በተመለከተ አንድ የስራ አስፈፃሚ አባል ለአራት አመት ከአገለገለ በኃላ በድጋሚ ለቀጣይ አራት አመት ብቻ ሊመረጡ እንደሚችሉ በመመሪያው ፀድቋል ።
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ በሌሎች የመመሪያው አንቀፆች ላይ ተወያይቶ መመሪያውን አፅድቋል ።
በውይይይቱ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር እና የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ዶክተር ሂሩት ካሳው፣ የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩር ፣ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ዱቤ ጅሎን ጨምሮ ሚኒስትሮች፣ የክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነሮች እና ሌሎች የምክር ቤቱ አባላት መገኘታቸውን ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.