Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ ከ725 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድና የጎርፍ መከላከያዎች እየተገነቡ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድሬዳዋ አስተዳደር ከ725 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመንገድና የጎርፍ መከላከያ ግንባታዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡

በከተማዋ እየተገነቡ ያሉት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በተለይም ከዚህ ቀደም ይስተዋሉ የነበሩ የትራፊክ መጨናነቆችን ከመፍታት ባለፈ÷ ለኢኮኖሚው መነቃቃት አይነተኛ አስተዋፆ እንደሚኖራቸው የድሬዳዋ መንገዶች ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ  አቶ ደረጄ ፀጋዬ ተናግረዋል።

ከተማዋ ለጎርፍ ተጋላጭ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ አሁን ላይ እየተገነቡ ያሉት የጎርፍ መከላከያ ግንቦች ህብረተሰቡን ከጎርፍ ስጋት ነፃ እንደሚያደርጉትም ነው አቶ ደረጄ የተናገሩት፡፡

ከዚህ ባለፈም በመንገድ፣ የውሃና ፍሳሽ እንዲሁም በቴሌኮም መሰረተ ልማታ ግንባታ ወቅት የሚስተዋለውን የመናበብ ችግር መቅረፍ ያስፈልጋልም ብለዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር እየተነቡ ያሉ አዲስ የመንገድ ፕሮጀክቶች እንዲሁም የነባር መንገዶች ጥገናና የጎርፍ መከላከያ ግንባታዎች መካሄዳቸው ለከተማዋ ነዋሪዎች በእጅጉ አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እየተሰሩ ባሉት ስራዎች ደስተኛ መሆናቸውን የከተማዋ ነዋሪዎች  ተናግረዋል።

ግንባታዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብተው መጠናቀቅ እንዳለባቸውም ነዋሪዎቹ መናገራቸውን ከከተማ አስተዳደሩ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.