Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽነር አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትጵያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ አምባሳደር ሞሃመድ ሳሊም አልረሺዲ ጋር ተወያይተዋል።
በውይይታቸው ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ በጋራ ስለሚሰሩባቸው ጉዳዮች መክረዋል።
በዚህም አገራቱ የሥራ ፈጠራ ዕድሎችን ለማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ ዘርፉን ለማዘመን በጋራ መስራት ስለሚችሉበት ሁኔታ በውይይቱ መዳሰሱን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.