Fana: At a Speed of Life!

160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) 160 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ ከየመን ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡
ከዛሬ ከተመለሱት 160 ስደተኞች ኢትዮጵያውያን መካከልም 42ቱ ባለፈው ሰኞ በጂቡቲ ከሰጠመችው ጀልባ የተረፉ መሆናቸውን ተመላክቷል፡፡
በዛሬው እለት የተመለሱት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የትራንስፖርት ወጭያቸውን በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የህዝብ፣ ስደተኞች እና ፍልሰት ዲፓርትመንት መሸፈኑ ተገልጿል፡፡
የድርጅቱ የዘመቻ እና ድንገተኛ ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጀፍሬይ ላቦቪትዝ÷በየመን በኩል የሚደረገው ህገ-ወጥ ስደት አደገኛ መሆኑን ጠቁመዋል።
በዚህም በባህር ላይ በሚደረግ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር በየጊዜው በርካቶችን ለህልፈት መዳረጉን ተናግረዋል፡፡
ሃላፊዋ አያይዘውም ስደተኞቹ ለመለወጥ ከሃገራቸው ቢወጡም የገልፍ ሃገራት በኮቪደ-19 ወረርሽኝ ክፉኛ በመመታታቸው ህልማቸው ምኞት ብቻ ሆኖ በጅቡቲ፣ ሶማሊያ እና የመን በችግር ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
ምንም እንኳ በኮቪድ-19 ምክንያት የስደተኞች ቁጥር መቀነስ ያሳየ ቢሆንም በስደት ላይ የሚገኙ ሰዎች የመን ሲደርሱ የሚገጥማቸው ችግር በፊት ከነበረው የበለጠ ውስብስብ መሆኑን አይኦኤም አስታውቋል፡፡
በዚህም ብዙዎቹ ህይወታቸውን በጎዳና ላይ ሲመሩ ሌሎች ደግሞ በእስር ቤት እና በደላላ እጅ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
አይኦኤም በአውሮፓውያኑ ከ2020 ግንቦት ወር ጀምሮ እስካሁን ድረስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 11 ሺህ ስደተኞችን ወደ አፍሪካ ቀንድ ሃገራት እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉም ነው የተገለጸው ፡፡
ባለፉት ሰባት አመታት በግጭት ውስጥ በምትገኘው የመን የሚገኙ ስደተኞችን ወደ ሃገራቸው ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት መንግስታት እንዲደግፉም ዳይሬክተሯ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ምንጭ፡-አይ ኦ ኤም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.