Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስብሰባን የተመለከተ ገለጻ ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አምባሳደሮች ተሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 5 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የውጭ ጉዳይ እና የውሃ ሚኒስትሮች ስብሰባ በተመለከተ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ ለሆኑ የአፍሪካ አገሮች አምባሳደሮች ገለጻ አድርገዋል።
ገለጻው በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ኪኒሻሳ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የተካሄደውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ስብሰባን የተመለከተ ሲሆን÷ በስብሰባው ውይይት የተደረገባቸውን ጉዳዮች እና የኢትዮጵያን ዕይታ ለአምባሳደሮቹ ገለጻ ተደርጓል።
ኢትዮጵያ በሶስቱም ሀገሮች ተቀባይነት ያለው ስምምነት ላይ ለመድረስ በአፍሪካ ኅብረት ማዕቀፍ ስር የሚደረገው ድርድር መቀጠል እንዳለበት በጽኑ እንደምታምን ተገልጿል።
ሶስቱ ሀገራት የአባይን ውሃ አጠቃቀም በተመለከተ ያላቸው አማራጭ በትብብር እና በአፍሪካዊ ወንድማማችነት ስሜት በጋራ መስራት እንደሆነ ለአምባሳደሮቹ አስረድተዋል።
ድርድሩን ስኬታማ ለማድረግ እና መተማመንን ለማጎልበት በአውሮፓውያኑ በጁላይ 2020 በአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባዔ የቢሮ ስብሰባ ወቅት በተደረሰው መግባባት እና በወጣው መግለጫ መሰረት በሁለት ደረጃ፣ በቅድሚያ በግድቡ የመጀመሪያ ሙሌት እና ተያያዥ የውሃ አለቃቀቅ ጉዳዮች እና በመቀጠልም ሁሉን አቀፍ የውሃ አጠቃቀም ስምምነት ማድረግ የተሻለ አማራጭ እንደሆነ ኢትዮጵያ እንደምታምን ገልጸዋል።
በቀጣዩ ሐምሌ ወር የሚደረገውን የሁለተኛ ዓመት ሙሌት አስመልከቶ ኢትዮጵያ ለሱዳን እና ግብጽ የመረጃ ልውውጥ ለማድረግ በቅን ልቦና ተነሳሽነቱን በመውሰድ በውሃ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስትር በኩል ለግብጽ እና ሱዳን አቻዎቻቸው ደብዳቤ የተላከ መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስትሩም ግብጽና ሱዳን የህዳሴውን ግድብ የአረብ አገሮች የውሃ ደህንነት ስጋት አድርገው የሚያቀርቡት ሁኔታ እንዳሳዘናቸው ገልጸው÷ የአባይ ተፋሰስ አገራት ሁሉ አፍሪካዊ ሆነው ሳሉ ጉዳዩን ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል የሚያራምዱት አቋም ተቀባይነት የሌለውና ሁሉም በአጽንኦት ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስበዋል።
ከታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ወቅታዊ የድርድር ሁኔታ በተጨማሪ ለአምባሳደሮቹ የኢትዮጵያ-ሱዳን ወቅታዊ የድንበር ሁኔታን በተመለከተ፣ ኢትዮጵያ ጉዳዩን በሰላማዊ መንገድ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተደረጉ ስምምነቶች እና ባሉት የድንበር አሰራር ማዕቀፎች አማካኝነት በድርድር ለመፍታት ያላትን ቁርጠኝነት ገልጻለች።
አምባሳደሮቹም በበኩላቸው ÷ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ድርድሩ በአፍሪካ ሕብረት ማዕቀፍ ስር “አፍሪካዊ መፍትሔ፣ ለአፍሪካ ችግር” በሚለው መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ ገልጸው ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በዚሁ ማዕቀፍ ድርድራቸውን እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።
የኢትዮጵያ-ሱዳን ድንበርን በተመለከተ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ ችግሮቹን ለመፍታት የወሰደችውን አቋም እንደሚያደንቁ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
+4
0
People Reached
83
Engagements
Boost Post
77
1 Comment
5 Shares
Like

 

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.