Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ጋር በአረንጓዴ ልማትና በህዳሴ ግድብ ድርድር ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የዉሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ በቀለ በኢትዮጵያ ከስዊድን አምባሳደር ሃንስ ሉንድኩዊስት ጋር ተወያዩ።

በውይይታቸውም ከኮቪድ 19 በኋላ የተሻለ ነገር መፍጠር በሚቻልበት እና በአረንጓዴ ልማት ዙሪያ ተወያይተዋል።

እንዲሁም ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን እና ግብፅ በታላቁ የህዳሴ ግድብ በቅርቡ ስላካሄዱት የሶስትዮሽ ውይይት ላይ ሀሳቦችን መለዋወጣቸውን በኢትዮጵያ የስዊድን ኤምባሲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በተጨማሪም በቀጠናው  ደህንነት ማረጋገጥ አስፈላጊነት ላይም ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺ እና አምባሳደሩ መክረዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.