Fana: At a Speed of Life!

ም/ከ ወ/ሮ አዳነች ለመሃመድ አል-አሩሲ ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 6 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዓለም አቀፍ መድረክ ስለታላቁ ህዳሴ ግድብ እና ተያያዥ ጉዳዮች ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያን አቋሞችን  በመወከል  የሚታወቀው መሃመድ ከማል አልአሩሲ ቤት በመገኘት  የአፍጥር ስነስርዓት ላይ ተካፈሉ።

እንኳን ለቅዱሱ የረመዳን ጾም አደረሳችሁ በማለት ለመሃመድ አልአሩሲና ለቤተሰቡ መልካም የፆም ወቅት እንዲሆንላቸው ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተመኝተዋል፡፡

በዓለም መድረክ ላይ ስለኢትዮጵያ የሚሟገተው መሀመድ አል አሩሲን ፤ ለአንተ ልዩ ክብር እና አክብሮት አለን ያሉት ምክትል ከንቲባዋ በከተማ አስተዳደሩ ስም እንኳን አደረሰህ ልንልህ የመጣነው በማለት ገልፀዋል፡፡

ይህን የጾም ወቅትም ሁሉም በሚችለው አቅሙ በአንድነት በመረዳዳት ማሳለፍ ይገባል ማለታቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.