Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ጤና ድርጅት በቀጠናው የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ማሰልጠን የሚያስችል ማዕከልን በአዲስ አበባ ከፈተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ጤና ድርጅት በቀጠናው የድንገተኛ ህክምና ባለሙያዎች ማሰልጠን የሚያስችል ማዕከልን በአዲስ አበባ መክፈቱን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ፊልድ ሆስፒታል የተገነባውን የስልጠና ማዕከል የጤና ሚንስትር ዶክተር ሊያ ታደሰና የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ማቲሾ ሞቲ መርቀው ከፍተዋል።

በስነ ስርአቱ ላይ ዶክተር ሊያ እንዳሉት የማዕከሉ መከፈት በዚህ የወረርሽኝ ወቅት የየዕለት ተግባር የሆነውን የድንገተኛ ህክምና ስራ ይበልጥ በዕውቀት እንዲመራ አቅም ይሆናል ብለዋል።

የዓለም ጤና ድርጅትም ማዕከሉን ለመክፈት ኢትዮጵያን በመምረጡ ማመስገናቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.