Fana: At a Speed of Life!

ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪሃት ካሚል ከዓለም የጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ዶክተር ማሺዲሶ ሬቤካ ሞቲን ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው የማህበረሰብ ጤና አገልግሎት፣ የጤናና የሰላም ጥብቅ ቁርኝት፣ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እንዲሁም ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ሚኒስትሯ በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጤናን ጨምሮ እየተከናወነ ስላለው የሰብዓዊ ድጋፍና ዜጎችን መልሶ የማቋቋም ሂደት ላይ ገለጻ አድርገዋል።

አክለውም የዓለም ጤና ድርጅት፣ ሌሎች የተባበሩት መንግስታት ፕሮግራሞች እና በአጠቃላይ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኢትዮጵያ አዳጋች ሁኔታዎች በገጠማት ጊዜ ሁሉ ለሚያደርጉት እገዛ ከልብ አመስግነዋል።

ዳይሬክተሯ በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የመሰረታዊ ጤና አጠባበቅ አገልግሎት ሽፋን ለበርካታ አመታት ሲከታተሉት የቆየ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በአጭር ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለ ዘርፍ መሆኑ ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ እንደሆነም ተናግረዋል።

በመጨረሻም በኢትዮጵያ ለሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞች የኮቪድ-19 ክትባት እንዲደርስ በመደረጉ በተባበሩት መንግስታት እና በሰራተኞቹ ስም ማመስገናቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.