Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

አደጋው ዋናውን መንገድ ስቶ የወጣ ተሽከርካሪ እግረኞችን በመግጨቱ የደረሰ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የመንገድ ትራፊክ አደጋ መከላከልና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

በአደጋው የሶስት ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ፥ አራት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው በደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ገልፀዋል።

የአደጋው መንስኤ ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ሲሆን፥ አሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ነው ብለዋል ዋና ኢንስፔክተሩ።

በሠላም አሰፋ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.