Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብን ፖለቲካዊ እና ዓለም አቀፋዊ ማድረግ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ውጤት ላይ አያደርስም – አቶ ደመቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴ ግድብ ድርድር የሚያስፈልገው ሂደቱን ፖለቲካዊ እና ዓለም አቀፋዊ ማድረግ ሳይሆን የመተመባበር ፣ መግባባት እና መዋሃድ መንፈስ ሊሆን እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአውሮፓ ሀገራት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ጋር በመተባባር በበይነ መረብ ባዘጋጁት ውይይት ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም በአፍሪካ ህብረት በሚመራው ድርድር ላይ ሁሉንም አሸናፊ የሚያደርግ ውጤት ላይ ለመድረስ ግብፅና ሱዳን ገንቢ የሆነ መንገድ ከተከተሉ የህዳሴ ግድብ ድርድር ጥሩ እድል ነው ብለዋል።

ሂደቱን ፖለቲካዊ እና ዓለም አቀፋዊ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለማድረግ መሞከር ኢትዮጵያ የቅኝ ግዛት ዘመን ስምምነቶችን እንድትቀበል አያደርጋትም ነው ያሉት።

አያይዘውም በአባይ ተፋሰስ ላይ ግብፅ እና ሱዳን የበላይ የሚያደርገውን  ፍትሃዊ ያልሆነ ስምምነት ኢትዮጵያ እንደማትቀበል መናገራቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የድርድር ቡድን አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ይልማ ስለሺ በበኩላቸው፥ ግብፅና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ከማድረግ ይልቅ ውሃ የመጋራት ጉዳይ ላይ ማተኮራቸውን አንስተዋል።

ኢትዮጵያም የመጭውን ትውልድ የመልማት ፍላጎት ችግር ላይ የሚጥል ስምምነት አትፈርምም ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.