Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 153 ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)- በክልሉ የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ 153 ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ።

በዕውቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኝሁ ተሻገር በክልል ደረጃ ለተመዘገበው አመርቂ ውጤት መሳካት ተሳትፎ ለነበራቸው አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

የተለያዩ ፈተናዎችን አልፈው ከፍተኛ ውጤት በማስመዘገብ ለክልሉ ኩራት ለሆኑ ተማሪዎች ምስጋና ያቀረቡት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ይልቃል ከፍአለ፣ ብዙ መስራት ከተቻለ ከዚህ በላይ ውጤት ማስመዝገብ እንደሚቻል ተናግረዋል።

ባለሀብቶችም ከአራት ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብ ማበረታቻ ለተማሪዎች አድርገዋል።

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ ተማሪዎች ቁጥር እያደገ መመጣቱን የተናገሩት ሀላፊው በዚህ ዓመት ከተፈተኑት 78ሺህ 870 ተማሪዎች መካከል 350 እና ከዛይ በላይ ያስመዘገቡት እንደ ክልል 66.1 በመቶ ነው ብለዋል።

በ2012/13 ዓ.ም ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ውጤት ካስመዘገቡ 153 ተማሪዎች ውስጥ 24ቱ ሴቶች ናቸው።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.