Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ የሚገኙ የግል ተቋማት እና ኩባንያዎች ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ሲልክሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል በዙሪያው ላሉት ነዋሪዎች በንጹሕ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ያደረገውን ድጋፍ ጎብኝተዋል።
በዚህ ወቅት ምክትል ከንቲባዋ እንደገለፁት የሲልክሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አስተዋፅኦ በማድረግ ያሳየውን ምሳሌነት አንስተው ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ውስጥ ያሉ ትልልቅ ተቋማትና ኩባንያዎች ማህበራዊ ሀላፊነታቸውን በመወጣት የሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታልን ተሞክሮ ሊተገብሩ እንደሚገባም ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጠቁመዋል ።
የሲልክ ሮድ አጠቃላይ ሆስፒታል ለማህበረሰቡ ነጻ የህክምና አገልግሎት ከመስጠት ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት በማገዝ ማህበራዊ ኃላፊነቱ እየተወጣ መሆኑንና በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ዶክተር ዋንግ ገልጸዋል ።
ሆስፒታሉ የከተማዋን የጤና ቱሪዝም መዳረሻነት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ተጨማሪ ዓለም አቀፍ የህክምና የልህቀት ማዕከል ለመገንባት እቅድ መያዙንም ስራ አስኪያጁ መናገራቸው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.