Fana: At a Speed of Life!

ህንድ በሀድያ ዞን የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ትደግፋለች – አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ህንድ በኢትዮጵያ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን እንደምትደግፍ በኢትዮጵያ የህንድ አምባሳደር ሮበርት ሼትኪንቶንግ ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ ከሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ጋር በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጉብኝት አድርገዋል፡፡

በሃድያ ዞን ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማጥናት የህንድ ባለሀብቶች መዋዕለ ነዋያቸውን በተለያዩ መስኮች እንዲያፈሱ ለማድረግ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥሩም አምባሳደሩ በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል፡፡

እንደ አምባሳደሩ ገለጻ ሀገራቸው በዞኑ በትምህርት፣ በጤናና በሌሎች ማህበራዊ ዘርፎች የሚከናወኑ የልማት ተግባራትን ትደግፋለች።

በተጨማሪም በማህበራዊ ዘርፍ የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ሀገራቸው ለማገዝ ፍላጎት እንዳላትም ነው ያስታወቁት።

በትምህርት መስክ ህንድ ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በጋራ እየሰራች መሆኗን አንስተው፤ በመምህራን ልማትና በቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ ድጋፍ ለማድረግ ስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንደገለጹት፥ መንግስት በኢትዮጵያና ህንድ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር በትኩረት እየሰራ ይገኛል።

የህንድ ባለሀብቶች በዞኑ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ተሰማርተው የስራ ዕድል መፍጠር የሚችሉበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ሚኒስትሯ አመላክተዋል።

የሀድያ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ ዶክተር አበበ ሎላሞ የዞኑ አስተዳደር በተለያዩ የልማት መስኮች መሰማራት ለሚፈልጉ የህንድ ባለሀብቶች አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.