Fana: At a Speed of Life!

ሶማሊያ ለምታካሂደው ምርጫ የአፍሪካ ህብረት ሂደቱን ማሳለጥ ላይ የመሪነት ሚና እንዲጫወት ጋበዘች

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆን የስልጣን ዘመን ለሁለት ዓመታት ያራዘመችው ሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት በቀጣይ በምታካሂደው ምርጫ የማስተባበሩን ሚና በቀዳሚነት እንዲወጣ ጋበዘች።

ፕሬዚዳንቱ  ሶማሊያ ለማካሄድ ያሰበችው ምርጫ ሰላማዊ ፣ አሳታፊ እና ወቅቱን የጠበቀ እንዲሆን  የአፍሪካ ህብረት የመሪነት ሚና እንዲኖረው መጋበዟን በትዊተር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

የአፍሪካ ህብረት ሶማሊያውያን ነፃ እና ፍትሃዊ በመሆነ መንገድ መሪዎቻቸውን በሚመርጡበት ምርጫ ላይ የማስተባበር ሚና  እንዲወጣ መጋበዙ ነው የተነገረው።

የሀገሪቱ መንግስት ለመጪው የሀገሪቱ ዴሞክራሲ ሁሉም ሶማሊያዊ በውይይቶች ላይ ተሳትፎ እንዲያደርግ ግብዣ አቅርቧል።

የሶማሊያ ፓርላማ ምርጫ ባለመካሄዱ የፕሬዚዳንት መሀመድ ፎርማጆን ስልጣን ባለፈው ሳምንት ለሁለት ዓመታት ማራዘሙ የሚታወስ ነው።

ይህን ተከትሎ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ፣ ምዕራባውያን ፣ አሜሪካ እና ብሪታኒያ የፕሬዚዳንቱ ስልጣን መራዘም ሶማሊያን ወደ ቀውስ የሚመራ ነው ሲሉ ውሳኔውን ተቃውመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.