Fana: At a Speed of Life!

የሲዳማ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት 5ኛ ዙር 1ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ስብሰባውን በሀዋሳ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድም ተመላክቷል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት  አፈ ጉባኤ አቶ ሰለሞን ላሌ በምክር ቤት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ላይ ÷የሲዳማ ህዝብ የፖለቲካ ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን የአደረጃጀት፣ አሰራርና የሰው ሃይል በሟሟላት ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዋል።

የህዝቡ ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱም  ህዝቡ ለለውጡ መንግስት ጥሩ አመለካከት መኖሩ ለክልሉ መረጋጋትና ሰላም ዋንኛ ዕድል መፍጠሩንም  ገልጸዋል።

አፈ ጉባኤው አያይዘውም 6ኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫም  ፍትሓዊ፣ ተዓማኒ ፣ ሰላማዊ እንዲሆን  እናና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሀገረ መንግስት መገንባት እንዲቻል የምክር ቤት አባላት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

ምክር ቤቱ የ2013 በጀት ዓመት የ9ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ማቅረብን ጨምሮ የተለያዩ ሰነዶችን ተወያይቶ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ታምራት ቢሻው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.