Fana: At a Speed of Life!

ኢድሪስ ዴቢይ በደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻድ ፕሬዚዳንት ኤድሪስ ዴቢይ በውጊያ ወቅት በደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተሰምቷል፡፡

የፕሬዚዳንቱ ህልፈት የተሰማው ከአማጽያን ጋር በነበረው ውጊያ የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው በኋላ ነው ተብሏል፡፡

ፕሬዚዳንቱ ከአማጽያን ጋር ውጊያ ላይ ያሉትን ወታደሮች ለመጎብኘት ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ጉብኝት ላይ ነበሩ ተብሏል፡፡

በሀገሪቱ ለስድስተኛ ጊዜ በተካሄደው ምርጫ 80 በመቶውን ድምጽ እንዳገኙ ተገልጿል፡፡

ይህም ለስድስተኛ ጊዜ ሃገራቸውን ለመምራት የሚያስችላቸው እንደነበር ተነግሯል፡፡

በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ ፓርላማ የተበተነ ሲሆን ወታደራዊ ምክር ቤቱ ለቀጣዮቹ አስራ ስምንት ወራት ሃገሪቱን እንደሚያስተዳድር አስታውቋል፡፡

በዚህም ልጃቸው ማሃመት ኢድሪስ ዴቢይ የሚመሩት ወታደራዊ ምክር ቤት ስልጣኑን መረከቡ ተገልጿል።

ባለ አራት ኮኮቡ ጄኔራል የ37 ዓመቱ ልጃቸው ማሃመት ኢድሪስ ዴቢይ የሚመሩት ወታደራዊ ምክር ቤት ፕሬዚዳንቱን ተክቷል ሲል የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል።

በቻድ ህገ መንግስት መሰረት በፕሬዚዳንቱ ላይ የሆነ ነገር ቢፈጠር ለ40 የሽግግር ቀናት ወይም እስከ ምርጫ ወቅት ሀገሪቱን የሚመራው የህግ አውጪ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ እንጂ ወታደራዊ ምክር ቤት አልነበረም ተብሏል።

ነገር ግን የተቋቋመው የሀገሪቱ ጦር ምክር ቤት ህግ አውጪው ሲበትን ፤ የሀገሪቱን ህገ መንግስት ማጠፉን ይፋ አድርጓል።

ይህም ወታደራዊ ምክር ቤቱ የራሱን ህገ መንግስት የመተካት ስራ እያከናወነ እንደሚገኝ ያመለክታል ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ፕሬዚዳንቱ በ1990ዎቹ በሀገሪቱ የተነሳውን አመጽ ተከትሎ ነበር ወደ ስልጣን የመጡት፡፡

 

ምንጭ፡-ቢቢሲ እና ሌሎች

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.