Fana: At a Speed of Life!

የጸሀፌ ትዕዛዝ ወልደመስቀል ታሪኩ መታሰቢያ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጸሀፌ ትዕዛዝ ወልደመስቀል ታሪኩ መታሰቢያ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ማዕከልን መርቀው ስራ አስጀምረዋል፡፡
ምክትል ከንቲባ እና የዩኒቨርሲቲው የቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በመርሐግብሩ እንደገለፁት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማረ ዜጋ ከማፍራት ጎንለጎን በጥናት እና ምርምር ስራዎች የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል ።
ዩኒቨርሲቲው በጸሀፌ ትዕዛዝ ወልደመስቀል ግቢ የኢትዮጵያን ቋንቋዎች እና ባህልን ለማዳበር እና ለትውልድ ለማስተላለፍም ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የጸሀፌ ትዕዛዝ ወልደመስቀል ታሪኩ የኢትዮጵያ ጥናት እና ምርምር ማዕከል 75 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገበት ጠቅሰው፥ የመማሪያ፣ የተማሪዎች ማደሪያ፣ ዘመናዊ ቤተ መፅሐፍት እና ልዩ ልዩ የምርምር ክፍሎችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል ።
በመርሐግብሩም በዩኒቨርሲቲው ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ እና በጥናት እና ምርመር ስራዎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ፕሮፌሰሮች እና የጸሀፌ ትዕዛዝ ወልደመስቀል ታሪኩ ቤተሰቦች የእውቅና እና የምስጋና ሽልማት እንደተበረከተላቸው ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.