Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በሶማሌ ክልል በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረው አምስተኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም (psnp 5) በዛሬው እለት በይፋ ተጀመራል ።

መርሃግብሩን የሶማሌ ክልል የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ከፌደራል የግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጅግጅጋ ከተማ አዘጋጅቷል፡፡

5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራም (psnp 5) ማስጀመሪያ ስነስርአት ላይ የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ፤ የተለያዩ የክልሉ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም ከክልሉ የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮና የግብርና ሚኒስቴር ሀላፊዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ተካሂዷል።

በስነስርአቱ ላይ ተገኝተው በክልሉ በቀጣይ አምስት አመታት የሚተገበረውን 5ኛውን ዙር የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራምን በይፋ ያስጀመሩት የሶማሌ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማን ናቸው::

በክልሉ ባለፉት አምስት አመታት የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ህብረተሰቡን በማሳተፍ የአፈርና የውሀ ጥበቃ ስራዎች በማከናወን ፤ የመንገድ ጥገናና የተለያዩ አገልግሎት መሰጫ ማዕከላትን በመስራት መርሀግብሩ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረጉን ተናግረዋል።

ባለፉት አምስት አመታት ተግባራዊ ሲደረግ በቆየው 4ኛው ምዕራፍ የልማታዊ ሴፍኔት ፕሮግራም አፈፃፀም የታዩ ክፍተቶችን በማሻሻል በቀጣይ ፕሮግራሙን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለቀጣይ አምስት አመታት ተግባራዊ የሚደረገው 5ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም ውጤታማ እንዲሁም ሁሉም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላቶች በቁርጠኝነት እንዲንቀሳቀሱ ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ አቅርበዋል።

በስነስርአቱ ላይ የ4ኛው ዙር የልማታዊ ሴፍትኔት ፕሮግራም አፈፃፀምና ቀጣዩ 5ኛው ዙር የፕሮግራሙ እቅድ ላይ ያተኮሩ የተለያዩ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ይካሄድባቸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.