Fana: At a Speed of Life!

በድርጅቱ አባላት መካከል የሚከሰቱ ልዩነቶችን በድርድር እንዲፈቱ ኢጋድ አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ዝግጁ ነው – የኢጋድ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በድርጅቱ አባላት መካከል የሚከሰቱ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈቱ ኢጋድ አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ያለውን ዝግጁነት የኢጋድ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ዖስማን ሃሰን ቢላል ገልጸዋል።

በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ በሱዳን የኢጋድ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ዖስማን ሃሰን ቢላል ጋር በቀጠናዊ የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱም አምባሳደር ይበልጣል በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ጉዳይ እና በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድርድር ሂደት የአገራችንን አቋም በዝርዝር ማስረዳታቸውን ከኢምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በሁሉቱም ጉዳዮች ያሉ ውዝግቦች በሠላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈቱና በቀጠናው ሰላምና ደህንነት ይረጋገጥ ዘንድ ኢትዮጵያ ያላትን ቁርጠኝነትና ዝግጁነት አረጋግጠዋል።

አምባሳደር ይበልጣል በገለጻቸው፤ ኢትዮጵያ በቀጠናው ሰላም መስፈን ኢጋድ ለሚጫወተው ገንቢ ሚና ያላትን ድጋፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

የኢጋድ ጽህፈት ቤት ዋና ኃላፊ ዖስማን ሃሰን ቢላል በበኩላቸው፤ በአምባሳደር ይበልጣል ለተደርገላቸው ገለጻ አመስግነው፤ ኢጋድ በድንበሩና በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ያሉ ልዩነቶችን በቅርበት እየተከታተለ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በድርጅቱ አባላት መካከል የሚከሰቱ ልዩነቶችን በሠላማዊ መንገድና በድርድር እንዲፈቱ ኢጋድ አዎንታዊ ሚና ለመጫወት ያለውን ዝግጁነትም ነው ዋና ሃላፊው የገለጹት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.