Fana: At a Speed of Life!

በይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን  በህግና ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው የሚገዙበት ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን  በህግና ስርዓት ማዕቀፍ ውስጥ ሆነው የሚገዙበት ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፣ በጠቅላይ አቃቢ ህግ እና በባለድርሻ አካላት መካከል ዛሬ ውይይት  ተካሂዷል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ረቂቅ መመሪያና የጥቆማና ቅሬታ አቀራረብ ረቂቅ መመሪያ ቀርቧል፡፡

የውይይት መድረኩ ብዙ የዘርፉ ተዋናዮች በተገኙበት የተካሄደ ሲሆን÷ በገለልተኛ አካል ለተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ግብዓት የሚሆን ሰፊ አስተያየት ለመሰብሰብ ያስቻለ ነው ተብሏል፡፡

በወቅቱም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መሐመድ ኢድሪስ ÷  የበይነ መረብ ሚዲያው በተመዝጋቢነት ፍቃድ አግኝቶ በህግ ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ ቢሰራ ህጋዊነት የሚያጎናፅፋቸው እድሎችን መጠቀም ያስችለዋል ብለዋል፡፡

እንደማሳያም በቅርቡ የፀደቀው የሚዲያ ፖሊሲ የመገናኛ ብዙኃን ዘረፉ የኢንቨስትመንት ጥቅማ ጥቅም እንዲያገኝና ከውጭ የሚገቡ የሚዲያ የፐሮዳክሽን እቃዎች ላይም የቀረጥ ማስተካከያ እንዲዲረግለት ጭምር እንደሚፈቅድ አብራርተዋል፡፡

ግዴታን መወጣት መብትን በይተኛውም ልክ ማግኘት ያስችላል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ÷ወደ ህጋዊነት ስትመጡ ባለሥልጣኑ እናንተን ለመደገፍ ሙሉ ትኩረት ይሰጣል ብለዋል ፡፡

በዚህ የዉይይት መድረክም  የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን እና የመገናኛ ብዙኃን ጥቆማና ቅሬታ አቀራረብ ረቂቅ መመሪያዎች ቀርበዉ ጠቃሚ ግብአት እየተሰበሰበባቸው ሲሆን በቀጣይ መመሪያዎቹን ለቦርድ አቅርቦ የሚያፀድቅ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ወደፊት በግልጽ በሚያወጣዉ ፕሮግራም መሰረት የበይነ መረብ መገናኛ ብዙሃን ምዝገባ፣ ፈቃድና እዉቅና የሚከናወን መሆኑን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.