Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው በትግራይ ክልል ከ134 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና መድሐኒትና ቁሳቁስ እያከፋፈለ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 12 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ መድሐኒት አቅራቢ ኤጀንሲ መቀሌ ቅርንጫፍ በትግራይ ክልል ለሚገኙ የጤና ተቋማት ከ134 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው የህክምና መድሐኒትና ቁሳቁስ እያከፋፈለ መሆኑን አስታወቀ።

የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ገብረማሪያም ÷ መድሐኒትና ቁሳቁስ እያከፋፈሉ ያሉት በክልሉ አገልግሎት እየሰጡ ለሚገኙ 50 የጤና ተቋማት ነው።

ቀደም ሲልም በክልሉ ለሚገኙ የጤና ተቋማት መድሐኒት ኤጀንሲው ሲያከፋፍል እንደነበርም አውስተዋል።

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ጤና ቢሮ የፋርማሲ አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ገብረእግዚአብሔር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው÷ የመድኒሐት አቅርቦት ኤጀንሲ እንዲሁም ጤና ሚኒስቴር የአካባቢውን ህብረተሰብ  ከበሽታ ተጋላጭነት ለመጠበቅ ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል።

ፍላጎቱ ከፍተኛ በመሆኑ ድጋፉ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.