Fana: At a Speed of Life!

የጤና ቀውስ የሚያስከትሉ መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰራጩ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ከፍተኛ የጤና ቁውስ የሚያስከትሉ መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ እየተሰራጩ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለሥልጣን አስታወቀ።

የባለሥጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሪት ሄራን ገርባ ህብረተሰቡ በተሳሳተ ግንዛቤ ከውጭ የሚገቡትን መድኃኒቶች ጥራታቸው ሃገር ውስጥ ከሚመረቱት የተሻሉ ነው ብሎ እንደሚያምን ጠቅሰው እውነታው ግን ከዚህ ይለያል ነው ያሉት።

በዓለም አቀፍ ደረጃ በአደገኝነት የተፈረጁ ምንም ፈዋሽ ንጥረ ነገር የሌላቸው ወይም የተሟላ ፈዋሽ ንጥረ ነገሮች የሌሏቸው መድኃኒቶች በህገ ወጥ መንገድ በአዲስ አበባ ከተማ ጭምር እየተሰራጩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ በተደረገው ጠንካራ የቁጥጥር ሥራ ንጥረ ነገሮቻቸው ከደረጃ በታች የሆኑ መድኃኒቶች በሃገሪቱ ስምንት በመቶ መሆናቸውን ነው ያስረዱት፡፡

እነዚህ መድኃኒቶች በድንበርና በአየር መንገድ በኩል በህገ ወጥ መንገድ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡

ነጋዴዎቹ ህገወጥ መድኃኒቶች በድብቅ በስልክና በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚስጥር እያሰራጩ በመሆናቸው ለመቆጣጠር ከባድና ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ጉዳይ ባለመሆኑ የሁሉም ህብረተሰብ ተሳትፎ እንደሚጠይቅ ዳይሬክተሯ ማሳሰባቸውን ኢፕድ ዘግቧል።ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.