Fana: At a Speed of Life!

ለጃፓናዊ ቢሊየነር ሚስት ለመሆን ከ20 ሺህ በላይ ሴቶች ማመልከቻ አስገቡ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለጃፓናዊው ቢሊየነር ዩሳኩ ማኢዛዋ የፍቅር ጓደኛ ለመሆን ያመለከቱት ሴቶች ከ20 ሺህ በላይ ደርሷል።

የሴቶቹ ማመልከቻ ቢሊኒየሩ ዩሳኩ ማኢዛዋ ወደ ጨረቃ ለሚያደርገው ጉዞ ውሃ አጣጫቸውን ይዘው መሄድ እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።

በኢሎን ሙሳክ የጠፈር ቴክኖሎጂ ኩባንያ በኩል ወደ ጨረቃ በመጓዝ የመጀመሪያው ግለሰብ የሚሆኑት ዩሳኩ ማኢዛዋ 9 ሚሊየን ዶላር ክፍያ በመፈፀም በርካታ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታዮችን ማፍራት ችለዋል።

በጉዞ ለመሳተፍ እና የቢሊየነሩ ውሃ አጣጭ መሆን የሚፈልጉ ሴቶችም የተለያዩ ጥያቄዎች እንደሚቀርቡላቸው ነው የተነገረው።

ከጥያቄዎቹ መካከል በግል ጄት የት መሄድ ትፈልጊያለሽ የሚለው ይገኝበታል።

በውጤታቸው መሰረትም ቢሊየነሩ ሲደሰትና ሲከፋ የሚያሳይ ፎቶ እንደሚቀርብላቸው ተጠቁሟል።

ምንጭ፦ ሬውተርስ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.