Fana: At a Speed of Life!

ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ ንቅናቄ በአዲስ አበባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ገቢ ማሰባሰቢያ በአዲስ አበባ ከተማ  ተጀመረ።

“ግድባችን የአንድነታችን እና የሉአላዊነታችን መገለጫ ነው” በሚል መሪ ቃል  የገቢ ማሰባሰቢያ እና የንቅናቄ ስራ በከተማዋ በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት እንደሚካሄድ ተገልፆል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት እና የኢትዮጵያ ታሪክ ባህልና ቅርስ አድን ድርጅት አዘጋጅነት የተጀመረው መርሃግብር ህብረተሰቡን በማነቃነቅ ለግድቡ የሞራልም ሆነ የገንዘብ ተሳትፎ እንዲያደርግ ለማስቻል መሆኑን ከከተማዋ ፕሬስ ሴክሪታሪያት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ታሪክ እና ቅርስ እንደመሆኑ ይህንንም በማስተዋወቅ  በመጪው ሀምሌ ወር ለሚደረገው ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ህብረተሰቡ የበኩሉን ድጋፍ እና ተሳትፎ እንዲያደረግ ከወዲሁ ለማነሳሳት መሆኑን የመርሃግብሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡

˝የህዳሴ ግድብ ጎዞ “በሚል በሀገር አቀፍ ደረጃ በተካሄደ የንቅናቄ እና የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር በ32 ከተሞችና በ200 ወረዳዎች   ከ11 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ  አቶ ደጀኔ ገ/ማርያም ገልጸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.