Fana: At a Speed of Life!

የ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም ይጀምራል ተብሎ የነበረው የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአንድ ወር ተራዝሞ  ጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚጀምር የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስታወቀ።

ፌዴሬሽኑ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር የክለቦችና የተጫዋቾች የምዝገባ ቀናትና የ2014 ውድድር መጀመሪያ ቀንን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።

በዚህም የየብሄራዊ ቡድኖች የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች አንድ ወር ወደፊት እንዲገፋ በመደረጉ የ2014 ዓ.ም ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ጥቅምት 7 ቀን 2014 ዓ.ም የሚጀምር ይሆናል በማለት ኮሚሽኑ በፌስቡክ ገፁ ላይ አስፍሯል።

እንዲሁም ከሀምሌ 1 እስከ ሀምሌ 15  ቀን 2013 የክለቦች ምዝገባ እና ከሀምሌ 1 ቀን 2013 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2014 የ2014 1ኛ ዙር የተጫዋቾች ዝውውር  እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.