Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በ8100 የሰበሰበውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በ8100 አጭር የፅሁፍ መልዕክት ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የሰበሰበውን ከ122 ሚሊየን ብር በላይ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስረክቧል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር በ8100 አማካኝነት ለግድቡ ግንባታ የሚውል ገንዘብ ከደንበኞቹ ሲያሰባስብ ቆይቷል፡፡
በዚህም ዛሬ ያሰባሰበውን 122 ሚሊየን 467 ሺህ 676 ብር ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስረክቧል፡፡

የተሰባሰበውን ገንዘብ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወይዘት ፍሬህይወት ታምሩ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻ አስረክበዋለል።

ወይዘሪት ፍሬህወት በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለፁት በ1ኛ ዙር 80 ነጥብ 3 ሚሊየን እንዲሁም በ2ኛ ዙር 49 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር ከደንበኞች ተሰብስቧል።

በአሁኑ የ8100 የ3ኛ ዙር የገቢ ማሰባሰብ ላይ 122 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር መሰብሰቡንና እስካሁን ከተሰበሰበው ገንዘብ እንደሚልቅ አስታውቀዋል።

በሶስቱ ዙሮች ከ252 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን በመጥቀስ ደንበኞች ስላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም በተቋሙና በሰራተኞቹ ስም 111 ሚሊየን ብር የቦንድ ግዢ ማከናወኑንም ወይዘሪት ፍሬህይወት ተናግረዋል።

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር  ዶክተር አረጋዊ በርሔ በበኩላቸው የግድቡ ግንባታ ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከ15 ቢሊየን ብር በላይ በቦንድ ግዢና በልገሳ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሸብር ባልቻም መላው ህብረተሰብ በ8100 በኩል ሲያደርግ ለቆየው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው የተጀመረው ድጋፍ ግድቡ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲቀጥልም ጥሪ ማቅረባቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.