Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ ስልጣን መያዣ መንገድ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ የምርጫ ስልት ብቻ ነው –  ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ስልጣን መያዣ መንገድ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ የምርጫ ስልት ብቻ ነው ሲሉ ተናገሩ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከሁለቱ ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመራጮች ምዝገባ ሂደት ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ ከሰላማዊ ስልት ውጭ ሌሎች አማራጮች የማያዋጡ እና ሊተገበሩ የማይችሉ ናቸው ብለዋል።

የመራጮች ምዝግባ በመጀመሪያዎቹ ሳምንታት በሚፈለገው ልክ ያልተከናወነ ቢሆንም ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

አሁን ባለው ሂደት ሲዳማ ክልል 80 በመቶ፣ አማራ 51 በመቶ፣ ኦሮሚያ 85 በመቶ፣ ቤኒሻንጉል ጉምዝ 70 በመቶ፣ ሐረሪ 55 በመቶ፣ ደቡብ 53 በመቶ፣ አዲስ አበባ 88 በመቶ፣ ድሬዳዋ 84፣ ሶማሌ 43 በመቶ በተከፈቱ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች መመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

በአፋር ክልል ከ453 ሺህ በላይ ሰዎች የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢብርቱካን ሚዴቅሳ የመራጮች ምዝገባው ባለፉት ቀናት በተሻለ መንገድ እየተከናወነ መሆኑን በውይይቱ ላይ ጠቅሰዋል፡፡

ሆኖም ምዝገባው በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ሊጠናቀቅ አንድ ቀን ብቻ በመቅረቱ ሁሉንም መራጭ ተደራሽ ለማድረግ መራዘሙ የማይቀር ነው ብለዋል፡፡

ቦርዱ እስከመቼ እንደሚራዘም እንደሚውስን ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብታቸውን ለመጠቀም በተቀረው ጊዜ ውስጥ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአልዓዛር ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.