Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ በበዓላት ወቅት የምርት እጥረት እንዳይከሰት ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) መጪዎቹን በዓላት ተከትሎ የምርት እጥረት እንዳይከሰት ግብረሃይል አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አባባ ንግድ ቢሮ ሃላፊ አቶ አብድልፈታ የሱፍ÷ የትንሳኤ እና የኢድ አልፈጥር በዓላትን መቃረብ ተከትሎ ገበያ ላይ የምርት እጥረት እንዳይከሰት ቢሮው ከተለያዩ ተቋማት ከተውጣጡ አካላት የተዋቀረ ግብረሃይል አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

በበዓላት ወቅት ከሌላው ጊዜ በተለየ ሁኔታ የዘይት፣ የዱቄት፣ የስኳር፣ የቁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋፅኦዎች ፍላጎት ስለሚጨምር ይህን ፍላጎት ለሟሟላት ዕቅድ ይዞ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በዚሁ መሰረት በኅብረት ስራ ማኅበራት በኩል የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በስፋት ለማቅረብ ስርዓት መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

ቢሮው በሕዝቡ ፍላጎት መጨመር ሳቢያ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ በማድረግ ገበያው እንዳይረጋጋ የሚያደርጉ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድም አስታውቀዋል።

በመሰረታዊነት በበዓላት ወቅት የምርት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ምርት ወደ ገበያ እንደሚገባና በዓላቱም በተረጋጋ የገበያ ሁኔታ እንዲከበሩ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን ሃላፊው ተናግረዋል።

ሸማቹ ማኅበረሰብም በበዓላት ወቅት ባዕድ ነገሮችን ቀላቅሎ የመሸጥ፣ ምርት የመደበቅና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ሲያጋጥመው ለሚመለከተው አካል በመጠቆም ይህን የሚያደርጉ አካላትን እንዲከላከል ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.