Fana: At a Speed of Life!

ከ6 ሺህ ከረጢት በላይ የ”ኦ” የደም ዓይነት መሰብሰቡን የደም ባንክ አገልግሎት አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደም ባንክ አገልግሎት በሶስት ሳምንት ውስጥ ከ6 ሺህ ከረጢት በላይ የ “ኦ” የደም ዓይነት መሰብሰቡን አስታወቀ።

የደም ባንክ አገልግሎት “ኦ” የተሰኘው የደም ዓይነት እጥረት ገጥሞት “ደም ለጋሾች ድረሱ” የሚል ጥሪ ለህብረተሰቡ አቅርቦ እንደነበር ይታወሳል።

ጥሪውን ተከትሎ በተገኘው ምላሽ አሁን ላይ ክምችቱን ወደ 15 ቀናት ከፍ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

አሁንም ቢሆን ያለው ክምችት ለ15 ቀናት ብቻ ስለሆነ ልገሳው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 211 ሺህ ከረጢት ከለጋሾች መሰብሰቡ ነው የተገለጸው፡፡

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው የፀጥታ መደፍረስ ችግር በበጀት ዓመቱ ደም ባንኮች በሙሉ አቅማቸው እንዳይንቀሳቀሱ ጫና ማሳደሩንም ተጠቁሟል።

“በአዲስ አበባ ልደታ እና በቂርቆስ ክፍለ ከተሞች እንዲሁም በመገናኛ፣ ሜክሲኮ እና አራት ኪሎ አደባባዮች ላይ ህብረተሰቡ ደም እንዲለግስ የማድረግ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል” ያሉት ዶክተር ተመስገን፤

በበክልሎች ያሉ ደም ባንኮች በበቂ ሁኔታ ከህብረተሰቡ ደም መሰብሰብ እንዲችሉ ግብዓቶች ከማሟላት በተጨማሪ የቴክኒክ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑንም ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.