Fana: At a Speed of Life!

የዘንድሮው ምርጫ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ነው-አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 14 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የዘንድሮው ምርጫ ለኢትዮጵያ አዲስ ምዕራፍ ነው ሲሉ የሲዳማ ክልል ፕሬዝዳንት  አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ።

ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብትን በመጠቀም  የምርጫ ካርድን በማውጣት  ለራሳቸውና ለሀገራቸው  ሲሉ ንቁ ተሳትፎ ሊደርጉ  ይገባል ብለዋል።

በክልሉ 2 ሺህ 2 17 የምርጫ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውን ጠቁመው÷ ነዋሪዎች ረዥም ርቀት ሳይደክሙ በያሉበት ለመራጭነት እንዲመዘገቡ መደረጉንም ገልጸዋል።

የምርጫ ሂደቱ የተሳካ እንዲሆንም ከባልድርሻ ተቋማትና አመራሮች ጋር ሰነድ ተዘጋጅቶ ምክከር መደረጉንም ነው ፕሬዚዳንቱ የገለጹት።

በዚህም የጸጥታናሰላም ሁኔታውን ምቹ ለማድረግ ከክልሉ  ህዝብ ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑንም  ተናግረዋል።

በሀዋሳ ከተማ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች የምርጫ ካርድን ሲያወጡ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያናገራቸው ነዋሪዎች ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።

እጅን አጣጥፎ በመቀመጥ ፍላጎትን ማሟላት አይቻልም ያሉት ነዋሪዎቹ÷ ለራስና ለሀገር የማሰብ አንዱ ተግባር መምረጥ መሆኑን ተናግረዋል።

በጌታሰው የሽዋስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.