Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከ 971 ሚሊየን በላይ  ችግኞች መዘጋጀታቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ከ 971 ሚሊየን በላይ  ችግኞች መዘጋጀታቸው ተገለጸ።

በተያዘው አመት ከተዘጋጁት ችግኞች ውስጥም  ከ25 ሚሊየን በላይ ያህሉን በጎረቤት  ሀገራት የሚተከሉ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች አስመልክቶ በጉራጌ ዞን በተካሄደ የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

በወቅቱም በደቡብ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ  እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ÷ በክልሉ ከ971 ሚሊየን በላይ ችግኞችን ማዘጋጀት እንደተቻለ ተናግረዋል፡፡

የፍራፍሬ የእንስሳት መኖ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞችን ማዘጋጀት ተችሏል ያሉት አቶ አንተነህ ÷የዝናቡን ስርጭት በመከታተል ለአካባቢ እንክብካቤ ልማት ስራው ስኬታማነት በትኩረት ይሰራልም ብለዋል፡፡

በክልሉ በበልግ እና በመኸር የአዝመራ ወቅት የአረንጓዴ አሻራን ተግባራዊ ለማድረግ የችግኝ ዝግጅት እና የጉድጓድ ቁፋሮ ስራ እየተከናወነ ነውም ነው ያሉት፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር የአፈር መሸርሸር እንዳይከሰት ከማድረግ ባሻገር የከርሰ ምድር የውሀ መጠን እንዲጨምር እያደረገ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የችኝኝ ዝግጅት ከሚደረግባቸው አካባቢዎች ውስጥ አንዱ የጉራጌ ዞን መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው በዘርፉ እየተካሄደ ያለው ሁሉን አቀፍ ጥረት ውጤታማ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ በፊት የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ ለውጤት ማብቃት እንደተቻለም ጠቁመዋል፡፡

እንደ አቶ አንተነህ ገለጻ የአረንጓዴ አሻራን መርሀ ግብር  ከሀገር ውስጥ ባለፈ ለኬንያና ለደቡብ ሱዳን ድጋፍ ለማድረግ  ታቅዷል ማለታቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.