Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ተወላጆች ምሁራን መድረክ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ክልል ተወላጆች ምሁራን መድረክ ተጠናቀቀ።
 
በምሁራን መድረኩ ላይ የክልል አደረጃጀት ጥያቄን በተመለከተ በቀረበ ፅሁፍ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
 
ምሁራኑ በክልሉ ህዝቦች የሚነሱ ጥያቄዎች ህገ መንግስቱን በተከተለ እና ወቅታዊ የሀገሪቱን ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ሊፈታ ይገባል ብለዋል።
 
በጥናቱ ባቀረቡት አማራጮችም ከህዝቡ ጋር ውይይት የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች የክልሉን ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ በሚሰጥ አግባብ ሊታዩ ይገባልም ነው ያሉት።
 
ሀገራዊ ለውጡ እንዳይደናቀፍ ምሁራን ሚና እንዲወጡ፣ የክልል ጥያቄ ትኩረት ቢሰጣቸው እና ህገ መንግስቱ የወቅቱን የሀገሪቱን ተግዳሮቶች መፍታት እንዲችል ዳግም ቢታይ የሚሉ ምክረ ሀሳቦችንም ምሁራኑ አቅርበዋል ።
 
መድረኩ የክልሉ የምሁራን ፎረምን ለሟቋቋም ኮሚቴ በማቋቋም ተጠናቋል።
 
በትናንትናው ዕለት በነበረው ውሎ ምሁራን ከዚህ ቀደም ልዩነትን በሚያሰፉ ስራዎች ላይ ልሂቃኑም ሆነ አመራሩ ማተኮራቸው አሁን ለሚታየው ችግር ምክንያት በመሆኑ በጋራ ለመቆም አንድነቱ ላይ በትኩረት እንዲሰራ ጠይቀዋል።
 
በሀይለየሱስ መኮንን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.