Fana: At a Speed of Life!

ሃገር አቀፍ የጸሎት እና የምህላ መርሃግብር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሃገር አቀፍ የጸሎት እና የምህላ መርሃግብር ተጠናቀቀ፡፡
ሃገር አቀፍ የጸሎት እና የምህላ መርሃግብሩ ከሚያዚያ 8 እስከ 14 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ሲካሂድ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በዚህም ዛሬ የመዝጊያ መርሃ ግብሩን መካሄዱን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በመርሃ ግብሩም ላይ የበላይ ጠባቂ አባቶች መልእክቶቻቸውን ያስተላለፉ ሲሆን የጤና ሚኒስቴር ዶክተር ሊያ ታደሰ ንግግር በማድረግ የጸሎት መርሃግብሩ የተሳካ እንዲሆን የነቃ ተሳትፎ ሲያደርጉ ለነበሩ አባል የሃይማኖት ተቋማት እና ሚዲያ አካላት የምስጋና የምስክር ወረቀት አበርክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.