Fana: At a Speed of Life!

ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የእንስሳት መድኃኒት ፋብሪካ ተመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ከ100 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በቢሾፍቱ ያስገነባው የእንስሳት መድኃኒት ፋብሪካ ተመረቀ።

የፋብሪካው ወደ ስራ መግባት ሃገሪቱ ለእንስሳት መድኀኒት የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ይቀንሳል ተብሏል ።

የብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ማርታ ያሚን በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ እንደተናገሩት ኢንስቲቲዩቱ የእንስሳት ክትባቶችን በማምረትና በማሰራጨት በተለይም ለግብርናው ዘርፍ ትልቅ እገዛ ሲያደርግ ቆይቷል።

ለተለያዩ ሃገራት የእንስሳት ክትባቶችን በመላክ የውጭ ምንዛሬ እያስገኘ መሆኑንም ገልጸው፤ ኢንስቲቲዩቱ ክትባቶችን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ ከማቅረብ ባለፈ በክትባት ዙሪያ ምርምርና ጥናቶችን እየሰራ ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ቢሾፍቱ የሚገኘው ብሔራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲቲዩት በ1956 ዓ.ም የተመሰረተ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.