Fana: At a Speed of Life!

የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት አስረኛ ዓመት በእስራኤል ተከበረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዳሴ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት አስረኛ ዓመት በእስራኤል መከበሩን በሀገሪቱ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታወቀ፡፡

በወቅቱ ከትውልደ ኢትዮጵያውያንና ከኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት ተካሄዷል፡፡

በእስራኤል የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ረታ ዓለሙ ግንባታው የደረሰበትን ደረጃ፣ ከኢትዮጵያውያን እና በትውልደ ኢትዮጵያውያን የተደረጉ ድጋፎችን አስታውሰዋል፡፡

አምባሳደሩ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ቤተ እስራኤላውያኑ የግድቡን ግንባታ ከዳር ለማድረስ ከአንድ ሚሊየን ዶላር በላይ ቦንድ የገዙ መሆኑን በመጥቀስ አሁንም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በመርሀ ግብሩ በእስራኤል የሕዳሴ ምክር ቤት ሊቀመንበር አቶ ራህሚም አላዛር የግድቡን ግንባታ ዳር ለማድረስ እስካሁን የተደረገውን ድጋፍ በሚመለከት ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ የተጠናከረ እንቅስቃሴ የሚደረግ መሆኑን አስታውቀዋል።

በመርሃ ግብሩ ኢትዮጵያውያንና ቤተ እስራኤላውያን ለግድቡ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ለመቀጠል ቃል መግባቸውን በእስራኤል ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.