Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር  ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ  ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሳዑዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር  ሌንጮ ባቲ ከሳዑዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ  አህመድ ቀጣን ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ፡፡

በውይይቱ በሁለትዮሽና ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም በዜጎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

እንዲሁም በውይይቱ ሁለቱ አገራት በሳኡዲ አረቢያ ማቆያ ቦታ ያሉ ተመላሽ ዜጎች ወደ አገራቸው በአፋጣኝ መመለስ እንዲችሉ በጋራ ለመስራት ከመግባባት  ላይ መደረሱን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.