Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ዘጠኝ ወራት በምዕራብ አሜሪካ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ600ሺህ ዶላር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በሎስ አንጀለስና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የልዑካን ቡድን ከልዩ ልዩ አደረጃጀት ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያኑ ሀገራቸውን ለማገዝ ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት በሎስ አንጀለስና አካባቢው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውን ለመደገፍ እያከናወኑ ስላሉት አርአያነት ያለው ተግባር አመስግነዋል፡፡
ይኸው ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ሀገሪቱ ከዳያስፖራዋ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም በላቀ ደረጃ ማግኘት እንድትችል ኤጀንሲው ከዳያስፖራው ጋር ተቀራርቦ መስራቱን እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡
በሎስ አንጀለስ የኢፌዴሪ ቆንስል ጀነራል አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል በበኩላቸው ዳያስፖራው ለሀገራዊ ፕሮጀክቶችም ሆነ ወቅታዊ ጥሪዎች እያደረገ ስላለው ድጋፍ አመስግነው ባለፉት 9 ወራት በምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ600ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡
ይህ ድጋፍም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ዳያስፖራው በሀገሪቱ ውስጥ እየተፈጠሩ ላሉ ችግሮች ምክንያት የሆኑትን ውስጣዊና ውጫዊ መንስኤዎች ተረድቶና ሀገሪቱ በለውጥ ሂደት ላይ ያለች መሆኗን ተገንዝቦ የለውጥ ሂደቱ እንዲሰናከል የሚፈልጉ ሃይሎች ባዘጋጁት ወጥመድ ውስጥ ሳይገባ ይህን አስቸጋሪ ጊዜ በድል ማለፍ እንዲቻል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማበርከቱን እንዲቀጥልም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.